ማህበረሰብ አቀፍ የፍትህ አገልግሎት መስጫ ከተማ...

image description
- ውስጥ Laws    0

ማህበረሰብ አቀፍ የፍትህ አገልግሎት መስጫ ከተማ አቀፍ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

መርሃ ግብሩ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የተካሄደ ሲሆን   የፍትህ ቢሮ ኃላፊ  አቶ ተክሌ በዛብህ፣የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀናን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና የሃገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ  ፍትሕን ማስፈን በቀዳሚነት የመንግስት ተቋማት ኃላፊነት  በመሆኑ የሚስተዋለውን የዘርፉን ስብራት ማሻሻል የሚገባ በመሆኑ የማህበረሰቡን ነባር ባህልና ሃገር በቀል እውቀቶችን በመጠቀም   ጠንካራ የዳበረ የፍትሕ ስርዓት በመዘርጋት መደበኛ የፍትህ ስርዓቱን እንዲያግዝ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም  በ2016 ዓ.ም ከአስር ሺህ በላይ የግል አቤቱታ ወንጀል መዝገቦች ለክስ ቀርበው  ስምንት ሺህ አምስት መቶ በላይ በእርቅ ማለቁን በ2017 ዓ.ምን በዘጠኝ ወራት ብቻ  ከዘጠኝ ሺህ ስምንት መቶ በላይ መዝገቦች ውስጥ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ በላይ  በእርቅ ማለቁን ጠቁመዋል።

አቶ ተክሌ   ግጭቶችን በእርቅ አፈታት ዘዴ እና በባህላዊ የእርቅ ስርአቶች መጠቀም  የሚባክነውን ኢኮኖሚ፣ ጊዜ ፣ጉልበት ለሌላ ልማት በማዋል የፍትህ አገልግሎት በማሻሻል የተጀመረውን ለውጥ ማገዝ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የአቃቂ ክ/ተማ ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በበኩላቸው ከሚከፋፍሉን እና ከሚለያዩን ነገሮች አንድ የሚያረጉን ብዙ ናቸው  አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ሁሉንም ወደፍርድ ቤት ከመውሰድ ሀገር በቀል እርቅ መፍቻዎችን መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።

በመጨረሻም ማህበረሰብ የፍትህ አገልግሎት የሚያስፈፅሙ ሀገር ሽማግሌዎች ተሰይመው በሕዴቱ ስልጠና በመስጠት መስሪያ ቦታ ተሰጥቷቸው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተጠናቋል፡፡

                                  ጥቅምት 20/02/2017


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.