
በህይወት ክህሎት ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የኤች አይቪ ኤድስ ሚኒስትሪሚንግ ፎካል ፐርሰን አስተባባሪነት በህይወት ክህሎት ዙርያ ለቢሮው ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት ከጤና ቢሮ ከመጡት የጤና ባለሙያ አቶ ስንታየሁ ጎሹ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን ሰዎች በተሰማሩበት የስራ መስክ ሁሉ ውጤታማና አትራፊ በሆነ መልኩ እንዲቀሳቀሱ የህይወት ክህሎቶች ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አቶ ስንታየው አክለውም ስለ ህይወት ክህሎት ምንነት፣ ጥቅሞቹና አይነቶቹ ፣ ውሳኔ ለመስጠት የሚረዱ ነጥቦች ፣ የመደራደር ክህሎት፣ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ክህሎት፣ የህይወት ግባችንን ስለማስቀመጥ ፣ የስነልቦናና የህይወት ክህሎት ውስጥ ራሳችንን ስንገመግም ምን ምን ማስቀመጥ እንዳለብን ሰፋ ባለ መንገድ አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም ሰልጣኞች ስለተሰጣቸው ግንዛቤ በማመስገን ለተነሱት ጥያቄና አስተያየት አቶ ስንታየሁ ጎሹ ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
ሰኔ 02/2017
ፍትህ ቢሮ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.