
በአዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ ስልጠና ተሰጠ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የህግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ከየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
መድረኩን የከፈቱት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የእቅድ እና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት አ/ቶ ማስረሻ ሀብቴ በመክፈቻ ንግግራቻም ስለ ስልጠናው አስፈላጊነት እና ምንነት በመግለጽ ሰልጣኞች ስልጠናውን ተከታትለው ወደተግባር መቀየር እንዲችሉ አሳስበዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ሰራተኛ የሆኑት በቃሉ ከበደ ሲሆኑ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 87/2017 ምንነት እና ስለ መንግስት ሰራተኞች መብት እና ግዴታ አሰልጠነዋል፡፡
በመጨረሻም ከሰልጣኞች ለተነሱ ጥያቄዎች አቶ በቃሉ ከበደ መልስ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡
5/10/17 ዓ.ም
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.