174/2016 ቄራዎች ድርጅት
የአዲስ አበባ ከተማ ቄራዎች ድርጅት የእንስሳት እርድ አገልግሎት መሥጠትና ሥጋና የሥጋ ውጤቶችን እንዲሁም ተረፈ-ምርቶችን አዘጋጅቶ ለሀገር ውስጥ እና ለውጪ ገበያ ጤናማ የሆነ እና ጥራቱን የጠበቀ ምርት በማቅረብ የከተማ አስተዳደሩን ገቢ ለማሳደግ እና
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልማት ድርጅቶች የሚመሩበትን ሁኔታ ለመወሰን ከወጣው ደንብ ቁጥር ፻፶፱/፪ሺ፲፮ ጋር ማጣጣም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሠን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀጽ ፷፰ ንዑስ አንቀጽ (፪) እና አንቀጽ ፺፫ ንዑስ አንቀጽ (፩) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡