ህትመቶች

175/2016 የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት

image description

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት የሰው መድሃኒትና የህክምና መሣሪያ አቅራቦት የጥራት ደረጃቸው የተጠበቀ እና ፈዋሸነታቸው የተረጋገጠ ለሰው አገልግሎት የሚውሉ መድሃኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን ለተገልጋዮች
በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርብ ማድረግ በማስፈለጉ፤ ይህም ለህዝቡ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልማት ድርጅቶች የሚመሩበትን ሁኔታ ለመወሰን ከወጣው ደንብ ቁጥር
፻፭፱/፪ሺ፲፮ ጋር ማጣጣም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሠን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮አንቀጽ ፷፰ ንዑስ አንቀጽ (፪) እና አንቀጽ ፺፫ ንዑስ
አንቀጽ (፩) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡