ህትመቶች

አዋጅ ቁጥር ፰/ ፪ሺህ፩ ዓ.ም. “የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ፤አስተዳደርና አመራር ማሻሻያ

image description

የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር የጤና አገልግሎት አሰጣጥ አስተዳደር አመራር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር በሚጣጣም መልኩ ማሻሻል በማስፈለጉ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር ፫፻፷፩/፲፱፻፺፭ /እንደተሻሻለ/ አንቀጽ ፲፬/1፩/ሀ/ እና /ረ/ በተደነገገው መሠረት ይህንን አዋጅ አውጥቷል፡፡ ፩. አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ ‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣ አስተዳደርና አመራር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር ፰/፪ሺህ፩›› ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ፪. ማሻሻያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጤና አገልግሎት አሰጣጥ አስተዳደርና አመራር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር ፩፻፰/፲፱፻፺፭ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡-