ህትመቶች

ደንብ ቁጥር 205/2018 የገላን ጉራ የኢንዱስትሪ ፓርክ ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ ደንብ

image description

በከተማው አስተዳደር የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርታማነት ለማሳደግ የተገነባውን ግዙፍ የኢንዱስትሪ ክላስተር በብቃት የሚያስተዳድር፣ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ ሁኔታ የሚያሳልጥ፣ የሚከታተል፣ የሚቆጣጠር እና በራሱ ገቢ የሚተዳደር ተቋም ማቋቋም በማስፈለጉ፤ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የተገነቡ ማምረቻ ሼዶች፣ የአገልግሎት ሕንጻዎች፣ የጋራ መሠረተ-ልማቶችና ሌሎች ንብረቶች በአግባቡ እንዲጠበቁ፣ እንክብካቤ እንዲያገኙ እና ዘላቂነት ባለው መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያስችል የተጠናከረ የአስተዳደርና የክትትል ሥርዓት የሚተገብር አደረጃጀት መኖር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤በኢንዱስትሪ ፓርኩ የለሙና ወደፊት የሚለሙ ሕንጻዎችና ፋሲሊቲዎች የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋግጥ የሚያስችል ሁኔታ መፍጥር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሠን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ ፺፫ ንዑስ አንቀጽ (፩) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡