ህትመቶች

አዋጅ ቁጥር ፷፯/፪ሺ፲፪ የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከልማቋቋሚያ አዋጅ

image description

ተፈጥሯዊ መዝናኛ ቦታዎችን ጨምሮ ለተለያዩ ተግባራት የሚውል ዘመናዊ የእፅዋት እንክብካቤና የኢኮቱሪዝም አገልግሎቶችን የሚሰጥ ማዕከል ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም በጉለሌና ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ክልል ውስጥ በሚገኘው መሬት ላይ ልዩ መልከዓ ምድርን ከፍተና ዋጋ ያላቸው የስነ ሕይወታዊ ሐብቶችና ለአደጋ የተጋለጡ ዝርያዎችን በዘላቂነት ለመንከበከብና ለልማት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ዘመናዊ የዕዕዋት ማዕከል ለማቋቋም ያስፈለገ በመሆኑ፣ እንዲህ አይነት የእዕዋት ማዕከል መቋቋም በስነህይወት በተፈጥሮ ሀብቶች አያያዝ እና በሌሎች አካባቢዎች መስኮች ላይ ለሚካሄድ ትምህርታዊና ምርምር ስራዎች አመቺ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ፣ እነዚህን ዓላማዎች ለማሳካትና የሕዝቡን የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤና ዘላቄታዊ የምርምር ተቋማት ጋር በትብብር መስራት ጠቃሚ መሆኑን በማመን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሸሻለ ቻርተር አዋጅ ቁጥር፫፻፰፩/፲፱፱፻፺፭ አንቀጽ ፲፬ (፩) (ሀ) መሰረት ይህንን አዋጅ አውጥቷል፡፡