146/2015 የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አደረጃት እና የፓራሚሊተሪ ሠራተኞች አስተዳደርን
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተፈጥሮ ወይም በሰው ሰራሽ ሊደርሱ የሚችሉ የድንገተኛ አደጋዎችን አስቀድሞ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስና ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ፤ አደጋ በሚከሰትበት ወቅት ውጤታማ የሆነ የአደጋ ምላሽ በመስጠት ህይወትና ንብረት ለማዳን እንዲሁም በአደጋ ምክንያት ለተጎዱ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለመስጠት እና በዘላቂነት መልሶ ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ፤ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖረውም የአደጋ ሠራተኛው በፓራ ሚሊተሪ ስርዓት ትዕዛዝ ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ተግባራትን በጥብቅ ዲሲፕሊን በመምራት አገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ ለማድረግ የአደጋ ሠራተኞችን አስተዳደር መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፸4/2ሺህ04 አንቀፅ ፵1 ንዑስ አንቀፅ ፳ እና ፺1 መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡