ህትመቶች

147/2015 የስትራቴጅክ ፕሮግራሞች ማኔጅመንት ጽህፈት ቤት ማቋቋሚያ

image description

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት፣ በተለይም የነዋሪውን በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ ሰው ተኮርና ትውልድ ተሻጋሪ ፕሮጀክቶችንና ፕሮግራሞችን በመንደፍና በመተግበር የበለጸገች ከተማን ለመገንባት መጠነ ሰፊ ርብርብ በማድረግ ላይ በመሆኑ፤የከተማው አስተዳደር ከንቲባ እና የበላይ አመራሮች በሚያመነጩዋቸው ሀሳቦች መሰረት ስትራቴጂክ እና ፖሊሲ ተኮር የሆኑ፣ በርካታ ባለድርሻዎችን በማቀናጀት አጋርና ተባባሪ አካላትን በማስተባበር የሚተገበሩ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ተቀርጸው በተለመደው አሰራር ወደ ስራ ሲገባ የተደራጀ የቴክኒክ እና ፖለቲካ አመራር ለመስጠት የሚያስችል የቅንጅትና የአመራር ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሆኖ በመገኘቱ፤ እነዚህ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች በአንድ በኩል ቅንጅትና ትብብር የሚሹ ስትራቴጂክ ጉዳዮችን በመለየት፣ ችግሮችን በመፍታትና ለከተማይቱ ራእይ ስኬት የሚረዱ ልምዶችን በመቀመር በማስፋትና በማበልጽግ መተግበር የሚገባ በመሆኑ፤አዳዲስ ፕሮግራሞች፣ ፕሮጀክቶችንና አሰራሮችን ከሌሎች የአገር ውስጥና የውጪ ልምዶች በመማርና በከተማ ደረጃ በመቀመርና ስራ ላይ በማዋል የአፈጻፀም ፍጥነትና ጥራትን ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ፤አዳዲስ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን የሚቀርጽና ለትግበራቸው የሚረዳ ሀብትን የሚያሰባስብ፣ ትግበራውን የሚያስተባብርና የሚመራ የስትራቴጂክ ፕሮግራሞች ማኔጅመንት ጽህፈት ቤት ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፸፬/፪ሺ፲፬ አንቀፅ ፺ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡