ህትመቶች

148/2015 የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ማስተግበሪያ የአደረጃጀት

image description

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህጻናት የወደፊት ተስፋ መሆናቸውን በማመን በከተማው ውስጥ ያሉ ሁሉም ህጻናት የተሻለ የህይወት ጅማሮ እንዲኖራቸው በማድረግ ለራሳቸው እና ለአገራቸው መጪ ዘመን መልካም እድል መፍጠር እንዲችሉ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣ሕጻናት በየእድሜ ደረጃቸው ሊደርሱበት በሚገባቸው የእድገት እርከን ላይ እንዲደርሱ ለማስቻል የተቀናጀና ሁለንተናዊ የአፈጻፀም አቅጣጫን በመከተል ተግባራዊ የሚደረግ ከጽንስ ወቅት ጀምሮ እድሜያቸው ስድስት አመት እስኪደርስ ድረስ ለሁሉም የከተማችን ህጻናት አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ በማስፈለጉ፣በከተማ አስተዳደሩ ውሳኔ መሠረት የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም ተቀርጾ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩና ይኸው ፕሮግራም ተገቢ የህግ ማእቀፍ ኖሮት መመራት እንዳለበት በመታመኑ፣በዚህም መሰረት የተጀመረውን የከተማችን የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም አደረጃጀትና አሰራር በመደንገግ የፕሮግራሙ አመራር፣ ፈጻሚና ተባባሪ አካላትን የሥራ ድርሻ እንዲሁም ኃላፊነትና ተግባራት በግልጽ መወሰን የአፈጻፀም አቅጣጫዎችና አሰራሮች መደንገግ በማስፈለጉ፣የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፸4/2ሺ04 አንቀፅ ፺1 መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡