149/2015 ውሃ አቅርቦትና የፍሳሽ አወጋገድ አገልግሎት ደንብ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የውሃ ፖሊሲ የከተማ የውሃ ተቋማት ሙሉ ወጪያቸውን እንዲሸፍኑ የሚያስገድድ በመሆኑ፤በአሁን ሰዓት ለህበረተሰቡ እየቀረቡ ያሉ አንድ አንድ አገልግሎቶች በአግባቡ የተጠና ታሪፍ የሌላቸው በመሆኑ፤የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃ አቅርቦትና የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት በመጠንና በጥራት እየሰፋ በመምጣቱ ወጪውን በመሸፈን የፋይናንስ አቋሙን በማሳደግ እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ አቅሙን በማሻሻል ቀልጣፋና አጥጋቢ የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችለው የታሪፍ ጭማሪ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ባለስልጣኑ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ግዴታቸውን በማይወጡ ደንበኞች ላይ ተጠያቂ የሚሆኑበትን አሰራር መዘርጋት እና በንብረቱ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመከላከል አጥፊዎቹ አግባብ ባላቸው ህጎች መጠየቃቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የሚጣልባቸውን አስተዳደራዊ መቀጮ እና የሚወሰድባቸውን አስተዳደራዊ እርምጃ በሕግ መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተሻሻለው አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ፶፩/ሺህ፱ አንቀፅ ፲፮ ንዑስ አንቀፅ (፩)፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፋይናንስ አስተዳደር ደንብ ቁጥር ፴፱/፪ሺህ፫ አንቀፅ ፳፫ ንዑስ አንቀፅ (፩) እና በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የአስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፸፬/፪ሺህ፲፬ አንቀጽ ፺፩ መሰረት ይህንን ማሻሻያ ደንብ አውጥቷል፡፡