ህትመቶች

ደንብ ቁጥር ፻፶፬/፪ሺ፲፭ የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ማቋቋሚያ ደንብ

image description

ደንብ ቁጥር ፻፶፬/፪ሺ፲፭ የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ማቋቋሚያ ደንብ የአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ዕድገትን ለማሳካት ቀልጣፋና ተደራሽ የብዙሃን ትራንስፓርት አገልግሎት ሰጪ ተቋም ማቋቋም በማስፈለጉ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተቀናጀ የብዙሃን ትራንስፓርት አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት በማቋቋምና የተቋሙን አደረጃጀት ለመወሰን ለከተማው ኀብረተሰብ የተሻለና ውጤታማ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ማቅረብ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሠን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፸፬/፪ሺ፲፬ አንቀጽ ፷፭ ንዑስ አንቀጽ (፭) እና አንቀጽ ፺ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡