ህትመቶች

ደንብ ቁጥር ፻፶፭/፪ሺ፲፭ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪን ለ፺ ቀናት ለማገድ የወጣ ማሻሻያ ደንብ

image description

ደንብ ቁጥር ፻፶፭/፪ሺ፲፭ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪን ለ፺ ቀናት ለማገድ የወጣ ደንብ ቁጥር ፻፳፪/፪ሺ፲፫ እንደገና ለማሻሻል የወጣ ደንብ በከተማው አስተዳደር ከግለሰብ የመኖሪያ ቤት ተከራይ የሆኑ ነዋሪዎች ላይ በአከራዮቻቸው ሚዛናዊ ከሆነው የቤት ኪራይ ዋጋ በላይ ጭማሪ እየተደረገ በመሆኑ አብዛኛው የከተማው ነዋሪ ተከራይ ለምሬት ከመዳረጉም ባሻገር የዋጋ ጭማሪው፣ ከአቅም በላይ የሆነ ኪራይ ማስከፈል፣ ተከራዮች ያለአግባብ በአከራዮቻቸው ፍላጎት ከተከራዩበት መኖሪያ ቤት እንዲወጡ ማድረግ፣ በአከራይ ተከራይ ግንኙነት አለመግባባት መፍጠሩ እና ለእንግልት መዳረጋቸው አሁንም የህዝብ እሮሮ እየቀረበበት በመሆኑ ችግሩ እስኪቃለል ድረስ በጊዜያዊነት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪን ማገድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤