157_አብርሆት_ቤተ_መፃሕፍት_ማቋቋሚያ_ደንብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ማቋቋሚያ ደንብ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ማቋቋሚያ ደንብ የከተማዋ ነዋሪዎች በእውቀት ላይ የተመሰረተ፣ በሞራል፣ በሥነ-ምግባርና በሥነ-ልቦና የታነፀ በሁሉም መስክ ብቃት ያለውና ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ለማፍራት ጥራት ያለው በአንድ ጊዜ በርካታ ሰዎች የሚታደሙበት የላቀ የንባብና የመረጃ አገልግሎት የሚያቀርብ ቤተ-መጻሕፍት ማቋቋም አስፈላጊነቱ ስለታመነበት፤ አለም አቀፍ ስታንዳርድ የሚያሟላ በቴክኖሎጂ የተደገፈና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ፣ ዓለም በዘርፉ የደረሰበትን የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሁኔታ መሰረት ያደረገ የቴክኖሎጂ ሽግግር ማመቻቸት፣ ተመራማሪ ትውልድ ለማፍራት የሚያስችል የንባብና ሁሉን አቀፍ የመረጃ ማዕክል ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ፤