ህትመቶች

ደንብ ቁጥር ፻፭፰/፪ሺ፲፮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የሠራተኞች አስተዳደር ደንብ

image description

ደንብ ቁጥር158/2016 የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የሠራተኞች አስተዳደር ደንብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተፈጥሮ ለገስ የሆነውን ውሱን የመሬት ሀብት ልማትና አጠቃቀም በቁጠባ፣ ግልጽ በሆነ አሰራር፣ ከሙስናና ከማጭበርበር በፀዳ ሁኔታ ለመምራትና ለማስተዳደር የሚችል ብቃት ያለው የሰው ሀብት እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በማግኘቱ፤ መሬት በማልማት፣ በማስተዳደር፣ በመቆጣጠር፣ በአጠቃላይ በመሬትና መሬት ነክ ንብረት አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት በአገልግሎት ሰጪና ተቀባይ መካከል የሚደረግ መመሳጠርን፣ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን፣ በሥልጣን አላግባብ መገልገልንና አድሏዊነትን በመጠቆም ተጠያቂነትን በማስፈን፤