ህትመቶች

ደንብ ቁጥር 159/2016 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልማት ድርጅቶች የሚመሩበትን ሁኔታ እንደገና ለመወሰን የወጣ ደንብ

image description

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለቤትነት በተያዙ የልማት ድርጅቶች ላይ የሚደረግ የቁጥጥር ሁኔታን ለማሻሻል እና የልማት ድርጅቶቹ የአሠራር ውጤታማነታቸውንና የፋይናንስ አቋማቸውን ለማጠናከር የሚያስችላቸውን እርምጃዎች መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የልማት ድርጅቶቹ ከግል ድርጅቶች ጋር በግልጽ ውድድር መሥራት የሚችሉበትን አቅም ለማጠናከርና ምርማነታቸውንና ትርፋማነታቸውን ለመጨመር ለንግድ ቅልጥፍና ያላቸውን አመለካከት የሚቀይር አመቺ የሆነ የቁጥጥር ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የልማት ድርጅቶቹ ተጠያቂነታቸውን በማረጋገጥና ግልጽነትን በማዳበር ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበትን ሥርዓት በመዘርጋት የኮርፖሬት አስተዳደራቸውን ከዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች ጋር ማጣጣሙ ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ፤ የልማት ድርጅቶችን የፋይናንስ አፈጻጸማቸውን ማሻሻል እና የፊስካል ስጋትንና በከተማ አስተዳደሩ ፋይናንስ ላይ የሚያሳድሩትን ጫና መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀጽ ፺፭ መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡