የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የማስረጃ አቀራረብ ስርዓት አፈጻፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2012
ባለስልጣን መ/ቤቱ በፍትህ አካላት ፊት የሚያቀርባቸውን ክሶችና አቤቱታዎች በማስረጃ አስደግፎ ሙግት ማካሄድ ለውጤት ማብቃቱ የሚታወቅ በመሆኑ ፣ የሚቀርቡት ክሶች በማስረጃ ጉድለት ምክንያት በሚሰጥ ፍርድ ባለስልጣን መ/ቤቱ መብትና ጥቅሙን እንዳያጣ እና የባለስሌጣኑን በፍትህ አካላት ዘንድ የሚቀርብበትን ማንኛውም አይነት ክሶችና አቤቱታዎች በአግባቡ እንዲከላከሌ እንዲሁም የባለስሌጣኑን መብትና ጥቅም በአግባቡ እንዲጠብቅ መደረግ ያለበት መሆኑ በመታመኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡