በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስልጣን፣ ተግባር እና ኃላፊነት ለመደንገግ የወጣ መመሪያ ቁጥር 4/2012
የባለስልጣን መ/ቤቱን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስልጣን፣ ተግባር እና ሃሊፊነት ለመወሰን እንዲሁም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን የአሰራር ሁኔታ፣ በጀት አጠቃቀም፣ የስራ ግንኙነትና የስራ አፈፃፀም መዘጋጀት የባለስልጣኑን የስራ አፈፃፀምና አገሌግሎት አሰጣጥ እንደሚያፋጥን በመታመኑ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዐስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡