ህትመቶች

1 PROCLAMATION NO.1-1985 የክልል አሰራ አራት መስተዳድር አዲስ ነጋሪ ጋዜጣ ለማቋቋም የወጣ አዋጅ

image description

አዋጅ ቁጥር ፩/፲፱፻፹፭ ዓ. ም. የክልል አሰራ አራት መስተዳድር አዲስ ነጋሪ ጋዜጣ ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የክልል አስራ አራት ክላዊ መስተዳድር በሕግ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር ለመወጣት የሚያስችሉ የራሱ ሕጎች በክልሉ ምክር ቤት ተመክረው የወጡና የሚወጡ በመሆኑ፤ በክልሉ ምክር ቤት የተለያዩ ሕጎች ኃይል ኑሯቸው ተፈጻሚ የሚሆኑት የሕጉ ተጠቃሚ የሆነው ሕዝብና የክልሉ መስተዳድር የሕግ አወጭ የሕግ ተርጓሚና የሕህግ አስፈጻሚ አካላት በሕዝብ ጋዜጣ በቅድሚያ አንዲያውቁት ሲደረግ ስለሆነ ሕጎቹ የሚወጡበት ኦፊሴል ጋዜጣ ማቋቋመ በማስፍለጉ፤ በክልል አስራ አራት የሽግግር መስተዳድር ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፳፪ መሠረት የሚከተለው ታውጅዋል። አንቀጽ ፩ ፩. አጭር ርአስ ይህ አዋጅ ‘’የክልል አስራ አራት አዲስ ነጋሪ ጋዜጣ ማቋቋሚያ አዋጅ’’ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል። አንቀጽ ፪ ፪. መቋቋም በዚህ አዋጅ ‘’አዲስ ነጋሪት ጋዜጣ’’ ተብሎ የሚጠራ የክልሉ መስተዳድድር ጋዜጣ ተቋቁሟል።