በአዱስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የንብረት አወጋገዴ አሰራርና አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 7/2012
የአዱስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስሌጣን የንብረት አወጋገድ ስርዓት ይበልጥ ግልፅና ቀሌጣፊ፣ ፍትሃዊና አድሎ የሌለበት እንዲሁም ንብረቶችን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በሚያስገኝ በተገቢ ተመጣጣኝ ዋጋ በተገቢው ጊዜና በተፈለገው ጥራት እንዱወገደ ለማድረግና እና የመ/ቤቱን ንብረት ውጤታማነት ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ጥቅም ላይ ማዋል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ ይህን የባለስልጣኑን ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ የንብረት አወጋገድ አሰራርና አፈጻጸም በተመለከተ የባለስልጣኑን ሰራተኞች ተግባርና ኃሊፉነት ለመወሰን እንዱሁም ፍትሃዊ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዐስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡