ህትመቶች

አዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከፍተኛ የውሃ ተጠቃሚ ደንበኞች የራሳቸውን አማራጭ የውሃ መገኛዎችን አጎልብተው እንዲጠቀሙ የሚያስችል መምሪያ ቁጥር 8/2012

image description

ባለስልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሚያቀርበውን ንጹህ የመጠጥ ውሃ በጥራትና በመጠን በማሳደግ ስርጭቱን ለማስፋት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በከተማው መስፋት እና የህዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያት የዉሃ ፍላጎቱ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ያለዉን ዉስን የዉሃ ምርት በከተማዉ ነዋሪ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለማከፋፈል በማስፈለጉ፡፡ በጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት በተቋቋመው ዴሊቨሪ ዩኒት በከተማዉ ዉስጥ የሚስተዋለዉን የውሃ እጥረት ችግር ለመፍታት ባለስልጣኑ በከፍተኛ ውሃ ተጠቃሚዎች የሚቀርበዉን የውሃ መጠን በመቀነስ ወደ ህዝቡ የሚሰራጨዉን የዉሃ መጠን እንዲጨምር ማድረግ ያለበት መሆኑ በመታመኑ ፡፡ ባለስሌጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የሚያቀርበዉን ንጹህ ዉሃ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማሰራጨት እንዲችል በከፍተኛ ውሃ ተጠቃሚዎች የሚያቀርበዉን የውሃ መጠን በመቀነስ ወደ ህዝቡ የሚሰራጨዉን የዉሃ መጠን ለመጨመር ይረዳው ዘንድ ከፍተኛ የዉሃ ተጠቃሚ ደንበኞች የራሳቸዉን አማራጭ የዉሃ መገኛ እንዲያጎለብቱ እና እንዲጠቀሙ ማድረጉ ያለው አስተዋፅዖ ከፍተኛ መሆኑ ስለታመነ ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷከል፡፡