በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃ ቆጣሪ ንባብ ሥራ የአሠራር መመሪያ ቁጥር 9/2012
ባለስልጣኑ ለእያንዳንዱ የውሃ አገልግሎት ደንበኛ በውል የውሃ ቆጣሪ በመግጠም የደንበኞችን አጠቃቀም በየወሩ በሚወሰድ ንባብ እና በባለስልጣኑ የውሃ ሽያጭ ታሪፍ መሠረት የየወሩን የአገልግሎት ክፍያ የሚሰበስብ ሲሆን ይህም ባለስልጣኑ በአዋጅ ተፈቅድለት ከሚሰበስባቸው ገቢዎች ዋንኛው እና በቀጥታ በውሃ ቆጣሪ ንባብ ጥራት ሊይ መሠረት ያደረገ በመሆኑ፡፡ የውሃ ቆጣሪ ንባብ ላይ የሚከሰቱት ችግሮች ደንበኞች ያልተጠቀሙበትን ከፍተኛ የውሃ ዋጋ እንደጠየቁ የማድረግ ፣ የደንበኞች ቆጣሪ በወቅቱ ሳይነበብ በመቅረቱ የተራዘመ ጊዜ የቆጣሪ ግብር ብቻ የሚጠየቁ እና ደንበኞች አጠቃቀም ከፍተኛ የታሪፍ ምደብ ውስጥ መግባት አላግባብ ከፍተኛ ክፍያ እንዲከፍለ የማድረጉ፣ አዱስ የውሃ ቆጣሪ የተገጠመላቸውን ደንበኞች የመጀመሪያ ንባብ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አለመነበቡ ደንበኞች የፍጆታ ሂሳባቸውን በወቅቱ ለመክፈል እንዲይችለ በማድረጉ እና ደንበኞች በየወሩ አንባቢው ያነበበውን ንባብ በንባብ ካርድ ሊይ በመመጻፉ ትክክለኛ ንባብ ስለመወሰደ ለማረጋገጥ ባለመጨቻላቸው በቆጣሪ ንባብ ስራ ላይ የግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲይኖር እንቅፋት በመፍጠሩ ባለስልጣኑ ይህን ዋነኛ ገቢውን በወቅቱ እንዲይሰበሰብ ከማድረጉም በላይ በደንበኞች ሊይ የመልካም አስተዳደር ችግር እየፈጠረ በመሆኑ፡፡ ይህንን የውሃ ቆጣሪ ንባብ ተግባር ችግር በመቅረፍ የንባብ ስራውን በጥራትና ተጠያቂነት በሰፈነበት ሁኔታ ለማከናወን የሚረዳ እና የደንበኞች የውሃ አገልግሎት ሂሳብ ክፍያን ከቅሬታ የፀዳ እንዱሁም የደንበኞችን እርካታ ባረጋገጠ ሁኔታ ለመፈጸም የሚያስችል እና ባለስልጣኑ ዋነኛ ገቢውን በጥራት እና በብቃት ለመሰብሰብ የሚያስችል አሰራር መኖር ያለበት መሆኑ በመታመኑ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡