ህትመቶች

4PROCLAMATION NO.4 -1995 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ማቋቋሚያ አዋጅ

image description

የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አዋጅ ቁጥር ፬/፲፱፻፺፭ ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የከተማው የዳኝነት አካል ሆነው በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር ፫፻፲፩/፲፱፻፺፭ የተቋቋሙ በመሆኑ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ሥራ አካሄድን በበላይነት የሚመራ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በማቋቋም የዳኝነት ነፃነትን በማረጋገጥ የዳኝነት አስተዳደርን ከማናቸውም አካል ወይም ባለስልጣን ተጽእኖ ነፃ በሆነ ሁኔታ እንዲመራ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣ በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር ፫፻፲፩/፲፱፻፺፭ ዓ.ም አንቀጽ ፵፬(፩) እና ፷፮(፪) በተደነገገው መሠረት የከተማው ጊዜያዊ አስተዳደር ይህንን አዋጅ አውጥቷል፡፡ ፩. አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፬/፲፱፻፺፭” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡