በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደረቅ ቆሻሻ አጓጓዥ ድርጅቶች የአሰራር መመሪያ ቁጥር 21/2013
በከተማችን አዲስ አበባ ከሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ ውስጥ 76 ፐርሰንት የሚሆነው በህብረት የሽርክና ጽዳት ማህበራት ከመኖሪያ ቤት የሚሰበሰብ ደረቅ ቆሻሻ ሲሆን ይህ ደረቅ ቆሻሻ ክፍያ ከተማው በሚሰጠው የመንግስት ተሽከርካሪ ስምሪት አማካኝነት ከጊዚያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማቆያ ቦታዎች እየተሰበሰበ ወደ ማስወገጃ ቦታ እንዲጓጓዝና እንዲወገድ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ነገር ግን በከተማው የሚመነጨው የደረቅ ቆሻሻ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ይህንን ደረቅ ቆሻሻ በመንግስት ተሸከርካሪ ብቻ ማጓጓዝ አዳጋች አድርጎታል፡፡ ስለዚህ ኤጀንሲው በከተማው በተለያዩ ምክንያት በህብረት የሽርክና የጽዳት ማህበራት፤ በመንገድ የጽዳት ሰራተኞች፤ በህብረተሰቡ የጽዳት ተሳትፎ፤ በምግብ ዋስትና በተደራጁ ሰዎች የፀዳና የተሰበሰበን ደረቅ ቆሻሻ እንዲሁም በህገወጥ መንገድ በየቦታው ተጥለው የተከማቹ ደረቅ ቆሻሻዎችን በተቀመጠው የማጓጓዝ ስታንዳርድ መሰረት ተጓጉዞ እንዲወገድ ለማድረግ እንዲሁም በዘርፉ የሚታዩ የደረቅ ቆሻሻ ማጓጓዝ ስርዓትን በተገቢው ሁኔታ ሌዩ ትኩረት ሰጥቶ ለማሻሻልና አሁን ያለውን ችግር ለመፍታት ያስችል ዘንድ በመንግስት ተሽከርካሪ ሲጓጓዝ የነበረን ደረቅ ቆሻሻ በኮንትራት ደረቅ ቆሻሻ ለሚያጓጉዙ ድርጅቶች እንዲሰሩት የሚስችል የአሰራር መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡