7 REGULATION NO. 7-2015 Auditor Negari gazzeta
ደንብ ቁጥር ፯/፪ሺ፲፭ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሠራተኞ አስተዳደር ደንብ መሥሪያ ቤቱ ኃላፊነቱን በገለልተኝነት እንዲወጣ ሠራተኞችን በነጻነት መቅጠር፣ ማስተዳደርና ማሰናበት የሚያስችል ደንብ ማውጣት በማስፈለጉ፤ የመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች ሙያዊ ነፃነታቸውን እና መብትና ግዴታቸውን በውል ለይተው በማወቅ ተግባራቸውንና ኃላፊነታቸውን ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ እንዲወጡ ለማድረግ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር ፫፻፷፩/፲፱፻፺፭ አንቀጽ ፲፩ ንዑስ አንቀጽ (፪) ተራ ፊደል (ሐ) እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁጥር ፸፯/፪ሺ፲፬ አንቀጽ ፳፰ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል