ህትመቶች

163/2016 የመሬት ይዞታ መብት ፈጠራ እና አገልግሎት አሰጣጥ ደንብ

image description

የከተማው አስተዳደር በመሬት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ የሚስተዋሉ የአደረጃጀት፣ አሰራር እና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ዕልባት ለመስጠት ለበርካታ ጊዜያት የመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ በማጥናት ወደ ሥራ የተገባ ቢሆንም አገልግሎት እየተሰጠባቸው የሚገኙት በርካታ መመሪያዎች ከተደረጉት የአደረጃጀት ለውጦች ጋር የተናበቡ ባለመሆናቸው እና መመሪያዎቹ በተበታተነ መልኩ የሚገኙ በመሆናቸው በውሳኔ አሰጣጥ፣ በሥራ ቅብብሎሽ በአጠቃላይ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ችግሮች በማጋጠማቸው፤ ችግሮቹን መፍታት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ችግሮቹን በማብራሪያና ሰርኩላር ለመፍታት ጥረት የተደረገ ቢሆንም ማብራሪያውና ሰርኩላሩ ከመብዛታቸው በተጨማሪ እርስ በእርሳቸው የሚጋጩበት ሁኔታ ስለተከሰተ የህግ ማዕቀፉን ማስተካከል በማስፈለጉ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የከተማን ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር ፯፻፳፩/፪ሺ፬ አንቀጽ ፴፫ ንዑስ አንቀጽ (፪) እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀጽ ፺፬ መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡