165/2016 የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ደንብ
ደንብ ቁጥር ፻፷፭/፪ሺ፮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አሰጣጥ ደንብ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት፤ የትራፊክ ፍሰትን ማስተካከል እና የትራፊክ አደጋን መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ቁጥር ፬/፪ሺ፮ አንቀፅ ፭ በተሠጠው ስልጣን መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡