ህትመቶች

ደንብ ቁጥር 166/2016 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብ

image description

ደንብ ቁጥር ፻፮/፪ሺ፲፮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብ የመንገድ መብራቶች በከተማዋ የማታ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች ከአደጋ እና ከወንጀል ድርጊት ተጠብቆ የሚንቀሳቀሱበት እና የመብራት አገልግሎት እንዳይቆራረጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በማንኛውም ሰዓት የሰዎች እንቅስቃሴ እንዲኖር እና ከተማዋ የቀን ብቻ ሳትሆን ሌሊትም የሚሰራባት ከተማ እንድትሆን በማስቻል ተጨማሪ እድሎችን ማስፋት በማስፈለጉ፤ በከተማዋ በዋና ዋና መንገዶች አገልግሎት እንዲሰጡ ተገንብተው በጥገናና እድሳት ምክንያት በተደጋጋሚ ጊዜ ለብልሽት የሚዳረጉትን በባለቤትነት ተከታትሎ ወደ አገልግሎት የሚመልስ አካል መፍጠርና ችግሩን በዘላቂነት መፍታት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ደረጃውን የጠበቀ ቴክኖሎጂ በተለይም የአካባቢ ጥበቃን የማይጎዳ፣ ደህንነትን የሚያረጋግጥና ኢነርጂን የሚቆጥብ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በከተማችን ውስጥ የመብራት አገልግሎት ሥርዓት በመዘርጋትና በመተግበር አለም አቀፍ ደረጃ በጠበቀ ሁኔታ ለከተማዋ ውበት ማራኪ ገጽታ በሚፈጥር መንገድ በማሻሻል፣ በማስተዳደር እና በመቆጣጠር፣ ወቅታዊ የጥገና ሥራዎችን በማከናወን የመንገድ መብራት በተደራጀ መልኩ የሚያስተዳደር ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀፅ ፺፫ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡