ደንብ ቁጥር 167/2016 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አደረጃጀት፣ አሰራር እና የፓራሚሉተሪ ሠራተኞች አስተዳደር ደንብ (ማሻሻያ) ደንብ
በከተማው ውስጥ የለሙ ፓርኮች፣ ኮሪደሮች፣ መንገዶችና ተጓዳኝ ሌማቶች ካላቸው ከፍተኛ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አከባቢያዊ ጠቀሜታ በተጨማሪ ለከተማችን ጽዳት፣ ውበትና መልካም ገጽታ የላቀ አስተዋጽኦ ያላቸው በመሆኑ ጽዳታቸውን፣ ውበታቸውንና መልካም ገጽታቸውን የሚያበላሹ ተግባራትን ለመከልከል፣ ለመቆጣጠርና አስተዳደራዊ እርምጃ ለመውሰድ በሚያስችል መልኩ ሥራ ላይ የቆየውን የደንብ ማስከበር ሕግ ማሻሻል አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፰፬/፪ሺ፲፮ አንቀጽ ፺፭ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡