ደንብ ቁጥር 177/2016 የአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ልህቀት ማዕከል

አዲስ አበባ ከተማ ህፃናትን ለማሳደግ ምርጥ የአፍሪካ ከተማ ለመሆኗ ራዕይ ይዛ በቀዳማይ የልጅነት እንክብካቤና እድገት ትግበራ ረገድ በአገር አቀፍ፣ በአህጉር፣ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ የተሞክሮ ማእከል ለመሆን እየሰራች ያለች በመሆኑዋ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ልሕቀት ማዕከሉን ስያሜ አህጉራዊ ስያሜ እንዲኖረው ደንቡን ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀፅ ፺፬ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህንን ማሻሻያ ደንብ አውጥቷል፡፡