ህትመቶች

181/2017 ፕላን ዝግጅት፣አፈፃፀም፣ክትትልና ቁጥጥር ደንብ ማሻሻያ ደንብ

image description

የአዲስ አበባ ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ረገድ እድገት እያስመዘገበ በመሆኑና ከሚመዘገበው ለውጥ ጋር አብሮ የአዲስ አበባ ከተማ ፕላን ዝግጅት፣ አፈፃፀም፣ ክትትልና ቁጥጥር ደንብ ማሻሻል በማስፈለጉ፤ መዋቅራዊ ፕላኑንና መዋቅራዊ ፕላኑን ለማስፈፀም የሚዘጋጁ ዝርዝር የፕላን ዝግጅቶችን እና አፈፃፀም በቅርበት የሚከታተል ፣ ከከተማዋ ነዋሪዎች አደገ ፍላጎትና አለምአቀፍ ተሞክሮ አንፃር እየቃኘ

ማሻሻያዎችን የሚያደርግ ከፕላን አዘጋጅ፣ ተግባሪ እና ተጠቃሚ የተዋቀረ የፕላን አመራር ቦርደ በአዲስ አበባ መዋቅራዊ ፕላን አዋጅ ቁጥር ፶፪/፪ሺ፱ መሰረት ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ መዋቅራዊ ፕላን አዋጅ ቁጥር ፶፪/፪ሺ፱ አንቀጽ ፴፱ ንዐስ አንቀጽ (፩) እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደ ር አስፈጻሚ አካላትን ሥለጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀጽ ፺፬ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህንን የማሻሻያ ደንብ አውጥቷል፡፡