ህትመቶች

183/2017 የብስክሌት መጋራት አገልግሎት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብ

image description

በአዲስ አበባ ከተማ የተሽከርካሪ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ምክንያት የሚያጋጥመውን የትራፊክ እንቅስቃሴ መጨናነቅ ለማቃለል፣ የከባቢ አየር ብክለት ለመቀነስ፣ ከቦታ ወደ ቦታ የሚደረግ እንቅስቃሴን ለማቀላጠፍ፣ ብስክለሌት በማሽከርከር የአካል ብቃትን ለማዳበር፣ የአእምሮ ዕዴገትን ለማጠናከር እና ጤናማ ዜጋ እንዲሆኑ ለማስቻለ የሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎትን ማስፋፋት አስፈላጊ በመሆኑ፤በከተማ አስተዳደሩ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ሥራ ለአጠቃላይ ከተማችን እድገት ገጽታ ግንባታና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ በተጨማሪ የብዙሃን ትራንስፖርት መሰረተ-ሌማቶች ችግርን የሚያቃልል እና የትራፊክ ፍሰቱን የሚያሻል በመሆኑ የተገነባውን የብስክልት መስመር በተሟሊ ሁኔታ አገልግሎት ላይ ለማዋል የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎት ለማስፋፋት የተገነቡትን የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውለ በማዴረግ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ወጭ ቆጣቢ፣ ተደራሽ፣ ፍትሀዊና ዘሊቂነት ያለው እናየማህብረሰቡን ፍላጎት ማሟላት የሚያስችል የብስክሌት ትራንስፖርት አገልግሎት የአሰራር ሥርዓት መዘርጋትና መቆጣጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀጽ ፺፬ መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡