ህትመቶች

185/2017 በምሽት የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የወጣ ደንብ.pdf

image description

የአዲስ አበባ ከተማ አሁን ከደረሰችበት ኢኮኖሚያዊና ማህበረሰባዊ ለውጥ አንፃር የአብዛኛው ማህበረሰብ የሥራ ባህል እና ፍላጎት በመለወጡ የንግድ ሥራዎችንና አገልግሎቶችን በምሽት መከወን እየተለመደ የመጣውን ተግባር ወጥነትና ቀጣይነቱን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤ በከተማዋ በስፋት እየተከናወነ የሚገኘው መሠረተ- ልማት በኢኮኖሚው ላይ የፈጠረውን መነቃቃት አጠናክሮ ለማስቀጥል፣ የሥራ ባህልን ይበልጥ ለማዳበር፣ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን፣ የከተማዋን ተወዳዳሪነት እውን ለማድረግ ቀን ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ በምሽት የንግድ እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤ በከተማዋ መንገድ ዳር ያሉ የንግድ ቤቶች እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት የሚያበሯቸው ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ መብራቶች የአካባቢውን ውበት ይበልጥ የሚያደምቁ እና ሠላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ አጋዥ በመሆናቸው ህብረተሰቡ ለመዝናናትና እረፍት ለማድረግ የሚያዘወትራቸው ተመራጭ ቦታዎች እንዲሆኑ ለማድረግ፤ የንግድና የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተቋማት በምሽት ተግባራቸውን ማከናወን የሚችሉበትን የአሰራር ሥርዓት በህግ መደንገግ በማስፈለጉ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀጽ ፺፬ መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡