ህትመቶች

አዋጅ ቁጥር ፮/፲፱፻፺፭ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአማካሪ ምክር ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ

image description

ጊዜያዊው የከተማው አስተዳደር ሲቋቋም ቀድሞ የነበሩት ምክር ቤቶች የፈረሱ ስለሆነ ለቀጣዩ የከተማው አስተዳደር የሕዝብ ምርጫ ነዋሪው ልምድ የሚቀስምበት መድረክ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤ በከተማው መልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ግንባታ ፅኑ መሠረት ሊይዝ የሚችለው በሂደቱ ነዋሪው በንቃት ሲሳተፍ በመሆኑ፤ የከተማው ልማት ሊረጋገጥ የሚችለው እና ነዋሪውም የልማቱ ተጠቃሚ የሚሆነው ነዋሪው በባለቤትነት መንፈስ ሲሳተፍ በመሆኑ፤ ለከተማው ነዋሪ የሚቀርቡ አገልግሎቶች ዓይነት፣ መጠንና ጥራት አስተማማኝ ሊሆን የሚችለው በነዋሪው ቀጥተኛ ተሳትፎ በመሆኑ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር በተሸሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር ፫፻፲፩/፲፱፻፺፭ አንቀጽ ፲፫/፩/ረ/ እና አንቀጽ ፷፮ (፪) እና ፷፮(፫)፩ (መ) መሠረት ይህንን አዋጅ አውጥቷል፡፡