193_2017 አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት ማቋቋሚያ ደንብ

የመንግሥት አገልግሎት ቀልጣፋ፣ አስተማማኝ እና ተድራሽ በማድረግ ወድ ተቀናጀ ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ደረጃ በየደረጃ በማሸጋገር የአገልግሎት አሰጣጥን፣ ፍትሃዊ፣ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ በማድረግ የዜጎችን ወጪና ጊዜ በመቆጠብ የተገልጋይ ዕርካታ ለማሳድግ የሚያስችል ተቋም ማቋቋም በማስፈለጉ፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር ፹፯/፪ሺ፲፯ አንቀጽ ፵፩ ንዑስ አንቀጽ (፭) መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡