195_2017 የመሬት ይዞታ መብት ፈጠራ እና አገልግሎት አሰጣጥ ደንብ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ አስተዳደር አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድላቸው ቦታዎችን የያዙ ነዋሪዎች መብት ተፈጥሮላቸው የይዞታ መብት ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ጊዜ የወሰዱ በመሆናቸውና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚያስችል ነባራዊ ሁኔታ ባለመኖሩ እና አገልግሎቱን ሰጥቶ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ፤
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀጽ ፺፬ መሰረት ይህን ማሻሻያ ደንብ አውጥቷል፡፡