ህትመቶች

196_2017 የኮሪደር እና የወንዞች ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን ለማቋቋም የወጣ ደንብ

image description

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ፤ ለኑሮ እና ለኢንቨስትመንት የምትመች እንዲሁም አህጉራዊ እና አለም-ዓቀፋዊ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን የሚያስችሉ ትውልድ ተሻጋሪ ፕሮጀክቶችንና ፕሮግራሞችን በመንደፍና በመተግበር የበለጸገች ከተማን መገንባት ላይ በመሆኑ፤ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች ከተማዋን አዲስ ገጽታ በማላበስ ውበትና ጽዳት ከማጎናጸፍም ባሻገር ከባቢያዊ አይበገሬነትና ዘላቂነትን በማረጋገጥና ሰው ሰራሽም ሆነ ተፈጥሮአዊ አደጋዎችን በመግታት ነዋሪው ደህንነቱ በተጠበቀ አካባቢ የመኖር ሕገ-መንግስታዊ መብት ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች ዝግጅት፣ ትግበራ፣ አስተዳደር፤ ክትትልና ድጋፍ፣ የነዋሪውን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚያስተዳድር ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ,4/፪ሺ፲፮ አንቀፅ -3 መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡