ህትመቶች

198_2017 በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሰው ኃይል ስምሪት በልዩ ሁኔታ ለማመጣጠን የወጣ

image description

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ እየታየ ያለውን የአፈጻጸም ክፍተት እና የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ በከተማ አስተዳደሩ በሶስቱም የአስተዳደር እርከኖች ላይ ተቋማት በአግባቡ ተልዕኳቸውን ለማሳካት የሚያስችል የተመጣጠነ የሰው ኃይል እንዲኖራቸው ለማድረግ የተጀመረውን የማመጣጠን ተግባር ለማከናወን ተጨማሪ ጊዜ የሚያስፈልገው መሆኑ በመታመኑ፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀጽ ፺፬ መሰረት ይህን ማሻሻያ ደንብ አውጥቷል፡፡