መሬት ለህዝብ ጥቅም ሲለቀቅ ካሳና ምትክ የሚሰጥበት እና የልማት ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት መመሪያ ቁጥር 79/2014
አዲስ አበባ ከተማ በርካታ የአለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ እና የአፍሪካ ህብረት መዲና ከመሆኗም በላይ አለም አቀፍ ቱሪስቶችን የምታስተናግድ በመሆኑ ስትቆረቆር በነበረው የኢኮኖሚ መዋቅር ፣ የዕውቀት ደረጃና ቴክኖሎጂ ፣ እንዲሁም የአኗኗር ባህል ላይ ተመስርቶ የተገነቡ ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ ግንባታዎች በስፋትና በብዛት የሚገኙበት የመሃሉ ከተማ ከዘመኑ የዕድገት ደረጃ ጋር የማይሄድና ለኑሮ ምቹ ባለመሆኑ መልሶ ማልማትን የሚጠይቅ በመሆኑ፤ ለልዩ ልዩ የልማት ስራዎች ማለትም ለመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ ለኢንቨስትመንትና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውል መሬት ማዘጋጀት ስለሚያስፈልግ ማልማት ስለሚገባና የመሬት ይዞታቸውን ለሚለቅ ባለይዞታ ተገቢና ተመጣጣኝ ካሳ ለመክፈል በነባሩ መመሪያ ያጋጠሙ ክፍተቶችን ከተሻሻለው አዋጅና ደንብ መሠረት ማስተካከል በማስፈለጉ፣ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት ሁኔታ ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1161/2011 እና ለሕዝብ ጥቅም ሲባል መሬት ሲለቀቅ ካሳ ስለሚከፈልበት እና ተነሺ መልሶ ለማቋቋም በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 472/2012 መሰረት የተካተቱ በርካታ ማሻሻያዎች በመኖራቸው ቀደም ሲል የነበረውን መመሪያ ቁጥር 19/2006 መተካት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዋጁ አንቀጽ 26 ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡