የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የአደረጃጀት እና የአሰራር መመሪያ ቁጥር 164/2017
በመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 መሠረት ተቆጣጣሪው አካል በሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው አከራይ ወይም ተከራይ የሚያቀርበውን አቤቱታ ተቀብሎ የተቆጣጣሪውን አካል ውሳኔ በከፊል ወይም በሙሉ እንዲፀድቅ ወይም እንዲሻር የሚወስን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጉዳይ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ በማቋቋም የኮሚቴውን አደረጃት እና የአሰራር ሁኔታ በግልጽ የሚደነግግ ህግ ማውጣት በማስፈለጉ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 አንቀጽ 24 ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡