ህትመቶች

172/2016 ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት

image description

የአዲስ አበባ ከተማ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ቀደም ሲል ሲሰራበት በነበረው የመንግስት ልማት ድርጅቶች ደንብ መሠረት ተቋቁሞ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ቢሆንም ሳይንሳዊ የአሰራር ሥርዓትን መሰረት አድርጎ ያልተደራጀ በመሆኑ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልማት ድርጅቶች የሚመሩበትን ሁኔታ ለመወሰን ከወጣው ደንብ ቁጥር ፻/፪ሺ፮ ጋር ማጣጣም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ ፊልም የማህበረሰባችንን አንድነትንና መልካም እሴቶችን ከማጠናከርና ከማልማት አንፃር የሚኖረው ፋይዳ
ከፍተኛነትን በመረዳት እና የባህል እሴቶችን ለከተማው ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፋይዳ የሚኖራቸውን ድርሻ ለማሳደግ እና ተወዳዳሪ ድርጅት እንዲሆን ለማስቻል፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሠን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬/፪ሺ፮ አንቀጽ  ንዑስ አንቀጽ (፪) እና አንቀጽ ፺ ንዑስ አንቀጽ () በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡