ክፍት የስራ ቦታዎች

አቃብያነ ህግ

የሥራ መግለጫ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ባለው ክፍት የስራ ቦታ በህግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያላቸውን በዜሮ አመት የስራ ልምድ እና ከአምስት አመት በላይ የስራ ልምድ ያላቸውን ሙያተኞች አወዳድሮ መቅጠር ስለሚፈልግ ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ማይጨው ክሊኒክ ጀርባ በሚገኘው ፍትህ ቢሮ አቃብያነ ህግ ጉባኤ 5ኛ ፎቅ በአካል ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት መመዝገብ ይችላሉ፡፡

እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

ተመዝጋቢዎች /ተወዳዳሪዎች/ ለምዝገባ ሲመጡ ሊያሟሏቸው የሚገቡ ሰነዶች ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ፓስፖርት የትምህርት ማስረጃቸውን ዋና ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር ከምትኖሩበት አካባቢ አግባብነት ካለው አካላት የተፃፈ የስነምግባር ማስረጃ፣

የምዝገባ ቦታ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ በሚገኘው ፍትህ ቢሮ አቃብያነ ህግ ጉባኤ 5ኛ ፎቅ በአካል ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እሁድ መስከረም 12ቀን 2017ዓ.ም በሚለው እትም ወጥቷል።

የሥራ መስፈርቶች

1ኛ ኢትዮጵያዊ የሆነች/የሆነ በኢትዮጵያ የሚኖር

2ኛ ለህገመንግስቱና ለህግ የበላይነት ተገዥ የሆነ

3ኛ የየትኛውም ፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ች እና ወንጀል ቅጣት የሌለበት፡፡

4ኛ በታታሪነቱ/ቷ/ በስነምግባሩ/ሯ መልካም ስም ያተረፈ/ች/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል/

5ኛ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም በህግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ የተመረቀ/ች

6ኛ የስራ ልምድ ዜሮ አመት በ2015 እና በ2016 የትምህርት ዘመን ተመራቂ ሆነው የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ ለወንዶች የመመረቂያ ነጥባቸው 3.5 እና ከዚያ በላይ ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች 3.25 እና ከዚያ በላይ

7ኛ ተፈላጊ የሰው ብዛት /15/ አስራ አምስት

8ኛ ከአምስት ዓመት በላይ የስራ ልምድ ላላቸው በአቃቢ ህግነት፣ በዳኝነት ፣ በህግ ምርምር ፣ በመምህርነት እና በተመራማሪነት ያገለገለ/ች/ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

9ኛ ተፈላጊ የሰው ብዛት ከአምስት ዓመት በላይ ላገለገሉ 10/አስር

10ኛ ደመወዝ በተቋሙ ስኬል መሰረት

11ኛ የስራ ቦታ ቢሮው በሚሰጠው ምደባ ቦታ፣

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ

አሁኑኑ ያመልክቱ