ህትመቶች

201_2018 የመንግሥት_ሠራተኞች_የዲሲፕሊን፣_ቅሬታና_ይግባኝ_አቀራረብና_አወሳሰን_ሥነ_ሥርዓት_ደንብ

image description

የከተማው አስተደር የመንግስት ሠራተኞች የዲሲፕሉን አፈፃፀምና የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት በተቀላጠፈ ፍትህ ሥርዓት መሰረት ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ፤ ‹ ግሌጸኝነትና ተጠያቂነት ያለበትን አሰራር እውን ለማድረግና ለቅሬታ አቅራቢዎች ፈጣን የሆነ ምላሽ በመስጠት ፍትሐዊ፣ ቀልጣፊ፣ ውጤታማ፣ ወጪ ቆጣቢ እና ተዳራሽ የሆነ አሰራርን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች የዲሲፕሊን አፈፃፀምና የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት ለመወሰን የወጣው ደንብ ቁጥር ፳፮/፪ሺ፪ን ተሻሽል ከወጣው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር ፹፯/፪ሺ፲፯ ጋር በማጣጣም መተካት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር ፹፯/፪ሺ፲፯ አንቀፅ ፻፶፪ ንዑስ አንቀፅ (፩) በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡