ህትመቶች

ደንብ ቁጥር 199-2018 የሥራ ተቋራጭ

image description

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየጊዜው እያደገ የሚካሂደውን የከተማ ነዋሪ ፍላጎት ለማርካትና የነዋሪውን ችግር ለማቅለል ሰፋፊ የሌማት ሥራዎችን ሲያከናውን ከግንባታ ሥራ አፈጻፀም እና ግብዓት አቅርቦት ጋር የተያያዙ በርካታ ችግሮችን እየፈታ በመሄዴ በከፍተኛ ሁኔታ ወጪ በመቀነስ በአጭር ጊዜ ውስጥ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ሌማት ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ልምድ የተወሰደበት በመሆኑ፤ይህንኑ ልማድ መነሻ በማድረግ በከተማው አስተዳደር የሚገነቡ የመኖሪያ ቤቶች፣ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ሌማት ሥራዎች በቁርጥ ነጠሊ ዋጋ ሊይ ተመስርቶ ድርድር በማድረግ ወጪን በመቀነስ፣ በአጠረ ጊዜ ውስጥ ጥራት ያለው ግንባታ ማስገንባት የሚቻል መሆኑ በመታመኑ፤ የሥራ ተቋራጭ ምልመላ ፍትሃዊ እና ተጠያቂነት ያለበት የሥራ ተቋራጭ የግንባታ ግዥና የሥራ ስምሪት የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለሕዝብ አገልግሎት ማቅረብ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥሌጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀጽ ፺፬ መሰረት ይህ ደንብ አውጥቷል፡፡