ህትመቶች

106_2011_የአዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር_የማህበራዊ_ትረስት_ፈንድ_ማቋቋሚያ_ደንብ

image description

መላውን ህብረተሰብ፣ ሲቪክ ማህበራት፣ የንግድ ዘርፉን እና በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበርና በማሳተፍ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር የተጋለጡና ውሎ አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎችን፣ ጧሪና ደጋፊ ያጡ አረጋውያንን፣ የአካልና የአዕምሮ ጉዳተኞችን፣ ያለወላጅ ወይም ያለአሳዳጊ የቀሩ ህጻናትን፣ የአልጋ ቁራኛ ሆነው ረዳት ያጡ ህመምተኞችን፣ እንዲሁም ለማህበራዊ ችግር ተጋላጭና ተጎጂ የሆኑ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት መርዳትና ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤በከተማው ውስጥ የነዋሪውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር በዘላቂነት ለማቃለል ለተቀረጹና ለሚቀረጹ ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ፣ የማህበራዊ ችግሮችን ለመከላከል፣ ተጎጂዎችን ለማቋቋም እና የስራ ፈጠራ ክህሎት ያላቸው ደሀ ሴቶችና ወጣቶችን ለመደገፍ እና በጎ ፈቃደኝነት ባህል እንዲሆን ለማበረታታት የማህበራዊ ትረስት ፈንድ ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር ፫፻፷፩/፲፱፻፺፭ (እንደተሻሻለ) አንቀጽ ፶፮ እና በከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፷፬/፪ሺ፲፩ አንቀጽ ፺፯ መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡