ህትመቶች

የዜጎች የስምምነት ሠነድ

image description

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2014 ዓ.ም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መልሶ ለማደራጀት በወጣ አዋጅ ቁጥር 74/2014 መሰረት ፍትህ ቢሮ እንደገና የተቋቋመ ሲሆን ከተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መነሻ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡ 

ይህንን ኃላፊነትም በብቃት ለመወጣት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማዘጋጀትና በማሟላት በተገልጋዮች ጥያቄና ፍላጎት መሰረት የላቀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የለውጥ ሂደቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ፣ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት ቢሮው በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ስርዓትን በዘላቂነት ለማስፈን እንዲችሉ፣ ቢሮው የተሰጡትን ተግባራት እና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችሉ ስልቶች ነድፎ የተገልጋዩን ፍላጎት የማርካት ስራ ለመስራት፣ እያንዳንዱ አገልግሎት የሚወስደውን ጊዜ መጠን አውቆ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስራ ለመስራት፣ የአገልግሎት አይነቱን መለየትና ደንበኞች ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታ አዉቀዉ ተገቢዉን አገልግሎት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ይህ የዜጎች የስምምነት ሰነድ  ተዘጋጅቷል፡፡