ደንብ ቁጥር 203/2018 በአደረጃጀት ክለሳ ጥናት ለተዘጋጁ የሥራ መደቦች የሠራተኞች የድልድል አፈፃፀም
የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ሌማት ኮርፖሬሽን በተቋሙ የሚሰጠውን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻልና የሕብረተሰቡን እርካታ ይበልጥ ከፍ ለማድረግ እንደገና የመዋቅራዊ አደረጃጀት ማሻሻያ በማድረግ ሠራተኞችን በማወዳደር ድልድል ማሰራት በማስፈለጉ፤ የሠራተኛ ድልድል ግልጽ፣ አሳታፊና ተጠያቂነት ያለበት አሰራር በመዘርጋት ሠራተኛውን በሥነ-ምግባርና በብቃት ላይ በመመርኮዝ ደረጃ በወጣላቸው መደቦች ላይ ድልድል ማድረግ በማስፈለጉ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር '7/2ሺ07 አንቀጽ )$2 ንዑስ አንቀጽ (1) መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷሌ፡፡