ደንብ ቁጥር 13/2018 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች ይግባኝ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ማለቀቅና ካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እንደገና ማቋቋሚያ ደንብ በመላው ኢትዮጵያ ተፈፃሚ የነበረውን ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፤ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን ወጥቶ የነበረውን አዋጅ ለማሻሻል የወጣውን አዋጅ ቁጥር ፬፻፹፩/፪ሺ፮ መሰረት በማድረግ በተሰጠ ውሳኔ ላይ ለአቤቱታ ሰሚ አካል አቤቱታ ቀርቦ በተሰጠው ውሳኔ ላይ የሚቀርብን ይግባኝ የሚቀርብበትና ውሳኔ የሚሰጥበት አሰራር በመዘርጋቱ ምክንያት በሥራ ላይ የቆየውን ደንብ በአዲስ መተካት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፤ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ በተመለከተ የተሰጡ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን በይግባኝ አይቶ ፈጣን፣ ውጤታማና ፍትሃዊ ውሳኔ በመስጠት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ማስቀረት የሚያስችል የይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እንደገና ማቋቋም እና አደረጃጀትና አሰራር መዘርጋት በማስፈለጉ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፤ ካሣ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፷፩/፪ሺ፪ አንቀጽ ፲፰ በተደነገገው መሠረት የመሬት ይዞታ ማለቀቅና ካሳ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ እንደገና ለማቋቋም ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡