ህትመቶች

አዋጅ ቁጥር ፲፱/፲፻፺፯ የከተማው አስተዳደር አካላት የአስተዳደሩ ቤቶች የማስተላለፍ ኃላፊነትና አፈፃፀሙን ለመወሰን የወጣ አዋጅ

image description

የከተማው አስተዳደር በግል ባለሀብቶችና አቅም ባላቸው ሌሎች ሰዎች በማህበርም ሆነ በተናጥል መኖሪያ ቤቶች እንዲገነቡ ቦታ አዘጋጅቶ በማቅረብና አስፈላጊ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የከተማው ነዋሪዎች ከፍተኛ የመጠለያ ችግር ለመቅረፍ እየሠራ ያለ በመሆኑ፣ ከዚህም ጎን ለጎን የመንግስትም ሆነ የግል ንብረት የሆኑና የመሠረት ልማት አገልግሎት በተሟላ ሁኔታ የማያገኙ ቤቶችን ተክቶ ከተማውን መልሶ በማልማትና በከተማው ውስጥ ከድህነት መግለጫዎች መካከል አንዱ የሆነውን የአብዛኛዎቹን የከተማውን ነዋሪዎች ከፍተኛ የመጠለያ ችግር ትርጉም ባለው መልኩ በመቅረፍ ከተማውን ተስማሚ የመኖሪያና የሥራ ከባቢ እንዲሆን ለማድረግ የከተማው አስተዳደር የከተማው ነዋሪዎች ያኗኗር ደፈጃና ፍላጎት ግምት ውስጥ አስገብቶ ባወጣው የቤት ልማት ፕሮግራም መሠረት ቤቶችን በመገንባት ላይ ያለ በመሆኑ፤ ፍትሐዊ፣ግልጽ፣ ቀልጣፋና ውጣ ውረድ በሌላው ቀላል በሆነ ሥነ-ሥርዓት፣ እንዲሁም የተጠቃሚዎችን የፆታ ተዋፅኦ በሚያረጋግጥና የገበያ አቅምን ግምት ውስጥ በሚያስገባ የክፍያ መጠንና የአከፋፈል ሁኔታ የተገነቡ ወይም የሚገነቡ ቤቶች ለከተማው ነዋሪዎች የሚተላለፉበትና የቤት ባለቤት የሚሆኑበት አፈፃፀም መደንገግ አስፈላጊ ሆነ በመገኘቱ፣ በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር ፫፻፷፩/፲፱፻፺፳ አንቀጽ ፲፬/፮/ሀ እና ፷፮/፪ መሠረት ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህንን አዋጅ አውጥቷል፡፡